Accessibility links

Breaking News

ዩናይትድ ስቴትስ ዴሞክራሲን ለመደገፍ ቁርጠኛ ናት


አምባገነዊነት አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ ተመልሶ እያቆጠቆጠ በመጣበት በዚህ ዘመን ዴሞክራሲ አገር መምራት የሚያስችልና ለህዝቦች ተጨባጭ ውጤት የሚያመጣ መሆኑን በግልጽና በማያሻማ ሁኔታ ማሳየት አለብን” ያሉት የአሜሪካ አለም አቀፍ ልማት አስተዳዳሪ ሰማንታ ፓወር ናቸው ይላል ርእሰ አንቀጹ ሀተታውን ሲጀምር፡፡

አምባገነኖች ትልቅ ኃይል ያለውን የተሳሳተ መረጃ በመርጨት ዲሞክራሲ የማያደርገውን ነገር እነሱ ያደረጉት መሆኑን እየሰበኩ ነው፡፡ “ ይሁን እንጂ ያ ትረካ ግን ሀሰት ነው፡፡” ብለዋል አሰተዳዳሪዋ፡፡

በርግጥም የቪዴም ተቋም እንዳመለከተው፣ አብዛኞቹ የዲሞክራሲ ተማራማሪዎች በ25 ዓመታት ውስጥ የዲሞክራሲን ፈለግ በተከተሉ አገሮች ላይ ባደረጉት ክትትል፣ ዴሞክራሲያዊዎቹ አገሮች የጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርታቸው 20 ከመቶ ማደጉን አስታውቀዋል፡፡

ለእነዚህ አገሮች ምጣኔ ሀብት ፈተና የሆነው ሙስና ነው፡፡ የምጣኔ ሀብት ልሂቃንና ብልሹ ፖለቲከኞች የራሳቸውን ጥቅሞች የሚያስከብሩባቸውን መረቦች በመጠቀም ዴሞክራሲን ከውስጥ ሆነው ሊቦረቡሩት ይችላሉ፡፡

ዩ.ኤስ.ኤድ ሙስናን ለመዋጋት፣ የተቀናጁ የጸረ ሙስና ሥራዎችን ለመደገፍና ለማጠናከር በመላ ተቋማቱ እየተጠናከረ ከመጣው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥረትና፣ ከፍትህ እንዲሁም ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የጸረ ሙስና ተቋም ግብረ ኃይል አቋቁሟል፡፡

ይህ ግብረ ኃይል ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ዘዴን የሚያቋቁም በመሆኑ የዩኤስ ኤድ ዘርፈ ብዙ ፕሮግራሞችን መክፈት ይችላል፡፡ ይህም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጥረት የሚደግፍ ሲሆን ጸረ ሙስና ማሻሻዮችን በማድረግ ለዴሞክራሲ መስፋፋት መንገድ ይከፍታል፡፡ ለዚህ ፈጣን ምላሽ ፕሬዛዳንት ጆ ባይደን አዲሱ የበጀት እቅድ 50 ሚሊዮን ዶላር መድቧል፡፡ዩኤ ኤስ ኤድምያ ገንዘብ ለተሳሳተ ዓላማ በዋለበትና በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የዴሞክራሲ ሂደት የሚጎዳ ሆኖ ከተገኘበት ከመንግሥት ተቋማት ሁሉ እያነሳ ወደ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ያዟዙራል፡፡

ከጸረ ሙስናው ባሻገርም አገሮች የሳይበር ደህንነታቸውን እንዲያጠናክሩ የተዛቡ መረጃዎችን እንዲመክቱ ከማድረግ ጋር የዴሞክራሲ ኃይሎች ራሳቸውን ከዲጂታል ስለላና ከሳንሱርና አፈና እንዲከላከሉ እንረዳልን ብለዋል አስተዳዳሪዋ ሰማንታ ፓወር፡፡

ዬ ኤስ ኤድ፣ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከዓለም አቀፍ የግሎባል ኤጄንሲ ተቋም፣ ጋር በመሆን ነጻና ክፍት የሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲስፋፋ፣ የዴሞክራሲ እሴቶችና የሰብአዊ መብት መርሆዎች ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር እንዲቀናጁ ከየአገሮቹ ጋር በመተባበር እየሰራ ይገኛል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታም ዩናይትድ ስቴትስ ትኩረቷን ነጻና ገለልተኛ የሆነ ሚዲያ በመላው ዓለም እንዲስፋፋበጨቋኝ መንግሥታትና በኢኮኖሚ ሁኔታዎች ችግር ላይ ያሉትን ጋዜጠኞችን በደገፍ ላይ አድርጋለች፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አምባገነን አገዛዞች እየተነሱ ቢመጡም ዲሞክራሲ ዛሬም ቢሆን በመላው ዓለም በጣም ተወዳጅና ተፈላጊ የሆነሥር ዓት ነው ብለዋል ሰማንታ ፓወር፡፡

በመጨረሻም ርዕሰ አቀንጹ ዩናይትድ ስቴትስ በየትኛውም የዓለም ክፍል ያሉት ህዝቦች ራሳቸውን እንዲያስተዳደሩና መሰረታዊ ነጽነትን እንዲጎናጸፉ ትደግፋለች ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG