Accessibility links

Breaking News

ዩናይትድ ስቴትስ የኮንፊሺየስ ተቋማትን የምትመለከተው እንደ ህዝባዊት ቻይና ሪፖብሊክ የውጭ መልክተኛ ነው


“በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የቻይና ቋንቋና ባህልን የሚማሩ ተማሪዎች፣ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ እና ወኪሎቹ ስውር መጠቀሚያ አለመሆናቸውን፣ ዩናይትድ ስቴትስ እርግጠኛ መሆን ትፈልጋለች” ይላል የዕለቱ ረእስ አቀንፅ ጽሁፉን ሲጀምር፡፡

እንደ ህዝባዊ ሪፖብሊክ ቻይና የውጭ መልዕክተኛ ሆኖ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚታወቀውና፣ በዩናይትድ ስቴት የኮንፊሺየስ ማዕከል፣ ወይም /CIUS/ እየተባለ የሚጠራው ተቋም፣ “የቤጂንግን ዓለም አቀፍ ፕሮፓጋንዳ ለማሰራጨትና የአሜሪካን የምርጫ ውጤት ለመወሰን፣ ከኮሌጅ ተቋማት አንስቶ፣ ከመዋዕለ ህፃናት እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ያሉትን፣ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምርህት ቤቶችን ይጠቀማል” ሲሉ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፓምፔዮ መናገራቸውን ርዕሰ አንቀጹ ያስረዳል፡፡

“የኮንፊሺየስ ተቋም በዋነኝነት፣ በቻይና መንግሥት የሚደጎም ነው” ያለው ርዕሰ አንቀጽ፣ ተቋሙ “የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የዓለም አቀፍ ተጽዕኖውን ለማሳደር የሚጠቀምበት የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ ነው” ብሏል፡፡

ይህ መግለጫ የወጣው፣ የኮንፊሺየስ ተቋማትንም ሆነ በኮሌጅና ዩኒቨስቲዎችን ውስጥ በተናጥል የሚገኙ የኮንፊሺየስ ድርጅቶችን ለመዝጋት አለመሆኑን ርዕሰ አንቀጹ ገልጿል፡፡

ይልቁንም፣ የኮንፊሸየስ ተቋም፣ እንደ ውጭ አገር የተልእኮ ተቋምነቱ፣ የቻይና ዜጎች የሆኑ ሠራተኞቹ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚያደርጉትን እንስቃሴያቸውን፣ አቀጣጠራቸውንና የገንዘብ ምንጫቸውን አስመልክቶ፣ ያለውን መረጃ፣ በየጊዜው ለውጭጉዳይ ሚኒስቴር፣ በግልጽ ማሳወቅ የሚገባው መሆኑን ለማሳሰብ” እንደሆነ፣ ርዕሰ አንቀጹ አስረድቷል፡፡

ይህ ዓይነቱ መረጃ፣ የዩናትድ ስቴትስ የትምህርት ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶቻቸው ውስጥ የሚካሄድ ተጽእኖ እንዳይኖር፣ ወይም በቤጂኒግ የሚደገፈውን ፕሮግራም ለተማሪዎቻቸው ማስተማር አለማስተማር ይችሉ እንድሆነ ለመወሰን፣ የሚያስችላቸውን ኢንፍሮሜሽን እንዲኖራቸው ያደርጋል” ብሏል ርእሰ አንቀጹ፡፡

ብሄራዊ የምሁራን ማህበር ወይም /the National Association of Scholars (NAS) / እንደሚለው ከሆነ በዩናይትድ ስቴትስ 75 የሚሆኑ የኮንፊሺየስ ተቋማት መኖራቸውን ርእሰ አንቀጹ አስታውቋል፡፡

ከመዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሚደርሱ ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ 500 የሚሆኑ የኮንፊሺየስ ክፍሎች ያሏቸው መሆኑን ጠቅሶ፣ ከእነዚህ አብዛኞቹ ፣ በዩንቨርስቲ ደረጃ ከተዋቀረው የኮንፊሺየስ ትምህርት ተቋም ጋር ግንኙነት እላቸው” ሲል ርእሰ አንቀጹ አመልክቷል፡፡

የቻይና መንግሥት፣ የኮሙዪኒስት ፓርቲ እና ርዕዮተ ዓለም በኮንፊሺየስ ተቋምና ፕሮግራም ላይ ያለው ተጽእኖ፣ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ፣ የዩናይትድ ስቴትስን ሲያሳስባት እንደቆየ፣ ርእሰ አንቀጹ አስታውሷል፡፡ ለምሳሌ እኤአ በ2017፣ ብሄራዊ የሳይንስ አካዳሚ እንዳስታወቀው፣ የኮንፊሽየስ ተቋማት ስር የሚገኙ ኣንዳንድ የትምህርት ተቋማት፣ ራሳቸውን በራሳቸው ሳንሱር እንዲያደርጉ ግፊት የነበረባቸው ሲሆን፣ በተቋማቱና በዩኒቨርስቲዎች መካከል የሚደረጉ ስምምንቶችም ይፋ ያልተደረጉ መሆናቸውን፣ ርእሰ አንቀጹ ገልጧል፡፡ አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች፣ የቻይንን መንግሥት እንዳይተቹ፣ የገንዘብ ችሮታ ይሰጣቸው እንደነበርና፣ የኮንፊሺየስ ተቋምም ስለቻይና የሰብአዊ መብት ረገጣ ሳያነሳ፣ የተመረጠ ታሪክ ብቻ እንደሚያስተምር፣ በርእሰ አንቀጹ ጽሁፍ ተጠቅሷል፡፤

ላለፉት አራት አስርት ዓመታት፣ ቤጂንግ በዩናይትድ ስቴት እንደልቧ በነጻ ስንትቀሳቀስ ኖሯለች፡፤ ያለው ርዕሰ አንቀጽ፣ ቻይና ግን በአንጻሩ ፣ ለዩናይትድ ስቴትስም ሆነ በአገሯ ለሚገኙ የውጭ አገር ዜጎች፣ ዝግ ሆና ቆይታለች ብሏል፡፡

በመጨረሻም፣ በዩናይትድ ስቴትስ የኤዥያ እና ፓስፊክ ጉዳዮች ኃላፊ ዴቭድ ስቲል ዌል፣

“የኛ ዓላማ ቻይና የግልጽነት፣ ክፍት የመሆንና የመጋራትን አስፈላጊነት እንድትረዳ ማድረግ ነው፣ ያ እስኪሆን ድረስ ግን ራሳችንን ለመከላከል የሚያስችለንን ሁሉ እርምጃ እንወስዳለን” በማለት የተናገሩትን በመጥቀስ ርዕሰ አንቀጹ ጹሁፉን ደምድሟል፡፡

XS
SM
MD
LG