Accessibility links

Breaking News

የዩናይትድ ስቴትስና ሜኮንግ ትብብር


US Deputy Secretary Stephen Biegun
US Deputy Secretary Stephen Biegun

እኤአ መስከረም 11/2020፣ የዩናትድ ስቴትስ፣ ካሞቦዲያ፣ ላኦስ፣ ማይናማር፣ ታይላንድ፣ ቬትናምና የኤዥያ የውጭ ጉዳይ ምኒስትሮች፣ የሜኮንግ ሥምምነት የተሰኘውን ትብብር ጀምሯል፣ ይላል የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ ሀተታውን ሲጀምር፤ ይህ አዲሱ ትብብር፣ የሜኮንግ ተፋሰስ አካባቢ ሃገራት፣ ለዩናይትድ ስቴትስ ያላቸውን አስፈላጊነት የሚያመላከት ሲሆን፣ እኤአ፣ በ2009፣ በታችኞቹ የሜኮንግ የተፋሰስ ሃገራት የጀመረው ትብብር፣ እያደገ ይሄዳል ብሏል፡፡ ርዕሰ አንቀጹ በመቀጠልም፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ “ለታችኞቹ የሜኮንግ ሃገራት ተነሳሽነት እየሠራን ያለውን ጥሩ ሥራና፣ ባለፉት 11 ዓመት፣ ለቀጠናው ያወጣነውን፣ የ$3.5 ቢሊዮን ዶላር እርዳታና ድጋፍ፣ አጠናክረን እንቀጥልበታለን” ማለታቸውን አስታውቋል፡፡

በሜኮንግ እና የዩናይትድ ስቴትስ ትብብር ምስረታ ስብሰባ ላይ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ለሜኮንግ አካባቢ ሃገራት፣ ከ150 ሚሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ የለገሰች መሆኗን ማስታወቅዋን፣ የርዕሰ አንቀጹ ጽሁፍ አመልክቷል፡፡ ከተጠቀሰው ገንዘብ ውስጥ፣ 52 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው፣ ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ማገገሚያ እንደሚውል፣ 55 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል፣ 33 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው ዘላቂና፣ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ገበያን ለማቋቋም፣ እንዲሁም 2 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው ደግሞ፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመዋጋት የሚውል መሆኑን፣ ርዕሰ አንቀጹ በዝርዝር አስረድቷል፡፡

የሜኮንግና የዩናይትድ ስቴትስ ትብብር፣ የራስ ገዥና የኢኮኖሚ ነጻነትን፣ የመልካም አስተዳደርን፣ የአገራትን ዘላቂ እድገትና ትብብርን ለማስፈን፣ መወሰኑን ርዕሰ አንቀጹ አስታውቋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ፣ “ በዩናይትድ ስቴትስ፣ ዓለምቀፍ የልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን አማካይነት፣ የኤዥያ ሃገሮችን የኢኮኖሚ እድገት ለመደገፍ፣ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ አውጥተናል፤ በመጭዎቹ ዓመታትም፣ ተጨማሪ ቢሊዮኖችን፣ ኢንቨስት ለማድረግ እቅድ አለን” ብለው መናገራቸው፣ በርዕስ አቀንጹ ጽሁፍ ተገልጿል፡፡

“ይሁን እንጂ፣ አሁን የገጠሙ ፈተናዎችን መጋፈጥ ይገባል፣ ይህም “ከቻይና ኮሙዩኒስቲ ፓርቲ የሚመነጨው፣ የሜኮንግ ተፈጥራዊ አካባቢዎችና የኢኮኖሚ ነጻነት ላይ፣ የተፈጠረውን ሥጋትና እየጨመረ የመጣውን አደጋ፣ መመከትን ይጨምራል” በማለት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማስጠንቀቃቸውን፣ የርዕሰ አንቀጹ ጽሁፍ አስታውቋል፡፡

“የቻይና ኮሙዩኒስት ፓርቲ፣ ወደ ተፋሰሱ ሃገራት የሚወርደውን ውሃ በማገድ፣ በተጠናል የወሰደው እርምጃ፣ ታሪካዊውን ድርቅ እንዲባባስ አድርጓል፡፡” ያለው ርዕሰ አንቀጽ፣

“ዩናይትድ ስቴትስ፣ ከተፋሰሱ ሃገራት ጎን በመቆም፣ የሜኮንግ ውሃ ኮሚሽን ያለውን የመረጃ ቋት፣ በግልጽ እንዲያጋራ፣ ትጠይቃለች ብሏል፡፡ ውጭ ጉዳዩ ሚኒስትሩ ማይክ ፓምፔዮ፣ “የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ፣ ስለ ውሃው ያለውን ዝርዝር መረጃ ለማጋራት፣ ቃል እንዲገባና ተጠያቂም እንዲሆን፣ የሜኮንግ ተፋሰስ ሃገራት፣ ግፊት እንዲያደርጉ እናበረታታለን” በማለት መናገራቸውንም፣ ርዕሰ አንቀጹ ይጠቅሳል፡፡ አያይዞም ፓምፔዮ “ያ የመረጃ ቋት፣ ለህዝብ መገለጽ አለበት፡፡ በየዓመቱም መለቀቅ ይኖርበታል፡፡ በሜኮንግ ወንዝ ኮሚሽን አማካይነት ለሁሉም መሰራጨት አለበት፡፡ ኮሚሽኑ የሜኮንግ አካባቢ ሃገራትን የሚያገልግል እንጂ፣ ቤጂንግን ብቻ መሆን የለበትም” በማለት ተናግረዋል ሲል፣ ርዕሰ አቀንጹ ጠቅሷቸዋል፡፡

ርዕሰ አንቀጹ በመቀጠል፣ ከመሠረተ ልማት ጋር የተገናኘው እዳ እና ፣ የቤጂንግ መንግሥት ይዞታ የሆኑት፣ ለምሳሌ እንደ ቻይና ኮሙኒኔሽን ኮንስትራክሽ ድርጅት የመሳሰሉት፣ መዝባሪና ስውር የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ውስጥ ያሉት፣ የመንግሥት ወኪሎች ድርጊት፣ ዩናይትድ ስቴትስን ያሳስባታል ብሏል ፡፡ ርእሰ አንቀጹ አክሎ፣ ሌላው አሳሳቢ ነገር፣ በአካባቢው እየተስፋፉ ያሉት ፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ አደንዛዥ እጽ፣ የሰደድ እሳት፣ ሲሆኑ፣ ብዙዎቹም፣ ከቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ የኢኮኖሚ ዞኖች ጋር ፣ግንኙነት ካላቸው ድርጅቶችና ኩባንያዎች የሚመነጩ ናቸው፣ ሲል አስታውቋል፡፡

በመጨረሻም፣ በሜኮንግና ዩናይትድ ስቴትስ ትብብር አማካይነት፣ አሜሪካ፣ አብረዋት የተባበሯትን ሃገሮች ጥቅም በማስጠበቅ፣ የሰላምን ዋስትናን ለማረጋገጥና፣ የበለጸገውን የሜኮንግ አካባቢን ለመጠበቅ ዝግጁ ናት፣ በማለት ርዕሰ አንቀጹ ጹሁፉን ደምድሟል፡፡

XS
SM
MD
LG