Accessibility links

Breaking News

ዩናይትድ ስቴትስ ወደ የዓለም የጤና ድርጅት አባልነት ተመለሰች


ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የርዕሰ-ብሄርነት ቃለ መሀላ እንደፈጸሙ ብዙም ሳይቆዩ፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ዩናይትድ ስቴትስን ከአለም የጤና ድርጅት አባልነት የማስወጣት ውሳኔን የሚቀለብስ ደብዳቤን መፈረማቸውን፣ የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ ጠቁሟል።

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካምላ ሀሪስ፣ ከዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር፣ በስልክ በተነጋገሩበት ወቅት፣ አሜሪካ ከዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት የመውጣትዋን ውሳኔ እንደምትቀለብስ፣ የገንዘብ መዋጮ ግዴታዋን እንደምትፈጽም እንዲሁም የዓለም የጤና ድጅትን ለማጠናከር በሚደረግ የማሻሻል ተግባር፣ በገንቢ አጋርነት እንደምትሰራ መግለጻቸውን፣ ርዕሰ-አንቀጹ አውስቷል።

ምክትል ፕሬዚዳንት ሃሪስ አያይዘውም፣ እሳቸውና ፕሬዚዳንት ባይደን፣ የዓለም የጤና ድርጅት፣ ኮቪድ-19ኝን ለመቆጣጠርና በዓለም ደረጃ የተሻለ የጤና ሁኔታን ለማዳበር እንዲሁም፣ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝን ለመከላከል፣ የተሻለ ዝግጁነት እንዲኖር ለማድረግ፣ ወሳኝ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው አስገንዝበዋል።

ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ በዓለም የጤና ድርጅት፣ 148ኛ የከፍተኛው ቦርድ ስብስባ ላይ የሚሳተፍ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ልኡካን ቡድን፣ አዲሱ መሪ እንዲሆኑ ተሰይመዋል። ፋውቺ በዓለም የጤና ድርጅት፣ ከፍተኛው ቦርድ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ “እኔም እንደሌሎቹ ተወካዮች፣ የዓለም የጤና ድርጅት ለዓለም አቀፉ ወረርሽን በዓለም ደረጃ የተሰተውለውን ምላሽ በመምራት በኩል ባለው ሚና አመስግነዋለሁ” ማለታቸውን ርዕሰ አንቀጽ ጠሷል።

“የባይደን አስተዳደር የተሻለ የዓለም የጤና ሁኔታ እንዲኖር፣ በሙሉ ልብ የመስራት ፍላጎት አለው፣ የዓለም የጤና ደህንነትንና የዓለም የጤና ደህንነት አጀንዳን ይደግፋል፣ ለሁሉም ሰዎች መልካም ጤና የተመላበት መጻኢ ዕድል የመገንባት አላማም አለው” ሲሉ፣ ፋው ቺ ማስገንዘባውቸውን ርዕሰ-አንቀጹ ገልጿል።

ዶ/ር ፋውቺ አያይዘውም፣ የባይደን አስተዳደር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሃገሮችም፣ ለኮቪድ-19 የክትባት መድሃኒ ተደራሽነት እንዲራቸው የሚጥረው፣ ኮቫክስ የተባለው ስብስብ አባል የመሆን እቅድ እንዳለው አስታውቀዋል። የክትባቱ መድሃኒት አንዲዳብር በዓለም ደረጃ የሚደረጉትን ጥረቶች፣ የምርመራና የህክምና ቁሶች ማከፋፈልን እንደሚደግፍ፣ በዓለም ዙርያ ልማት እንዲበረታም ይረዳል ማለታቸውን ርዕሰ-አንቀጹ አውስቷል።

ኮቫክስ የኮቪድ-19 የክትባት መደሃኒት ምርትን በማበራክትና በማዳበር፣ በዓለም ዙርያ ያሉት ሀገሮች ሁሉ፣ እኩል ተደራሽነት እንዲኖራቸው ዋስተና የመስጠት ዓላማ አለው። የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም ታድያ፣ “ዛሬ ለዓለም የጤና ድርጅትና ለዓለም ጤና መልካም ቀን ነው” ሲሉ፣ በትዊትውር ገጻቸው ደስታቸውን አገልጸዋል።

የዓለም የጤና ድርጅት የዓለም ሀገሮች ቤተሰብ ነው። ዩናይትድ ስቴትስ በቤትሰቡ አካልነት በመቀጥልዋ፣ ሁላችንም ደስተኞች ነን” ሲሉም አክለውበታል በማለት የዕለቱ ርዕሰ-አንቀጽ፣ ሀተታን አብቅቷል።

XS
SM
MD
LG